አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 7፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በነገው ዕለት የሚጀመረውን ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ በስኬት ለማካሄድ የተሟላ ዝግጅት ተደርጓል አሉ የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር መስፍን አርዓያ (ፕ/ር)፡፡
የመከላከያ ማርቺንግ ባንድ የሀገራዊ የምክክር ጉባኤውን ዋዜማ ምክንያት በማድረግ በአዲስ አበባ የተለያዩ አደባባዮችና ጎዳናዎች ደማቅ ትርዒት እያቀረበ ነው፡፡
መስፍን አርዓያ (ፕ/ር) በዚሁ ወቅት እንዳሉት፥ ኢትዮጵያ በታሪኳ ለመጀመሪያ ጊዜ ለምታካሄደው ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ አስፈላጊ ቅድመ ዝግጅቶች ተጠናቅቀው ዋዜማው ላይ እንገኛለን ብለዋል።
በዚህ ታሪካዊ ጉባኤ ላይ ከተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍሎች የተወከሉ 4 ሺህ በላይ ታሳታፊዎች በጋራ በመቀመጥ በሀገራቸው የጋራ ጉዳዮች ላይ በሰፊው ይመክራሉ ብለዋል።
ሀገርን በጽኑ መሠረት ላይ ለመገንባት በሚደረገው በዚህ ታሪካዊ ጉባኤ እያንዳንዱ ተመካካሪ በንቃት እንዲሳተፍ ጥሪ ማቅረባቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡

