አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 9፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የሊጉ ሻምፒዮን አርሰናል ክሪስቶስ ሶሊስን ከክለብ ብሩዥ ለማስፈረም ተስማምቷል፡፡
የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል ለተጫዋቹ ዝውውር 40 ሚሊየን ዩሮ እንደሚከፍል ዘ አትሌቲክ ዘግቧል፡፡
የ24 ዓመቱ የፊት መስመር ተጫዋቹ በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት ለክለብ ብሩዥ ባደረጋቸው 52 ጨዋታዎች 22 ግቦችን አስቆጥሮ 29 ለግብ የሚሆኑ ኳሶችን አመቻችቶ አቀብሏል፡፡

