Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

‎አንዲት እናት 6 ነጥብ 4 ኪ.ግ የምትመዝን ህጻን በሰላም ተገላገለች ‎

‎አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 23፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ‎በቤንች ሸኮ ዞን አንዲት እናት 6 ነጥብ 4 ኪ.ግ የምትመዝን ህጻን በሰላም ተገላግላለች።

‎በዞኑ የአማን ሻሸቃ ቀበሌ ነዋሪ የሆነችው ወ/ሮ ሳይሉሽ ባህሩ በሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ ማስተማሪያ ሆስፒታል የህክምና ባለሙያዎች በተደረገላት ክትትል ህጻኑን በቀዶ ህክምና መገላገሏን በሆስፒታሉ የማህጸንና ጽንስ ስፔሻሊስቱ ዶ/ር ቹቹ አረጋ ገልጸዋል።

‎ወ/ሮ ሳይሉሽ ባህሩ በተመሳሳይ ከ6 ዓመት በፊት 2ኛ ልጇን ስትወልድ 5 ኪ.ግ መሆኑንና በቀዶ ጥገና ህክምና እንደተገላገለች ገልጻለች።

በ‎ተስፋየ ምሬሳ

Exit mobile version