አንዲት እናት 6 ነጥብ 4 ኪ.ግ የምትመዝን ህጻን በሰላም ተገላገለች
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 23፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በቤንች ሸኮ ዞን አንዲት እናት 6 ነጥብ 4 ኪ.ግ የምትመዝን ህጻን በሰላም ተገላግላለች።
በዞኑ የአማን ሻሸቃ ቀበሌ ነዋሪ የሆነችው ወ/ሮ ሳይሉሽ ባህሩ በሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ ማስተማሪያ ሆስፒታል የህክምና ባለሙያዎች በተደረገላት ክትትል ህጻኑን በቀዶ ህክምና መገላገሏን በሆስፒታሉ የማህጸንና ጽንስ ስፔሻሊስቱ ዶ/ር ቹቹ አረጋ ገልጸዋል።
ወ/ሮ ሳይሉሽ ባህሩ በተመሳሳይ ከ6 ዓመት በፊት 2ኛ ልጇን ስትወልድ 5 ኪ.ግ መሆኑንና በቀዶ ጥገና ህክምና እንደተገላገለች ገልጻለች።
በተስፋየ ምሬሳ