Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ኦሮሞ በታሪኩ የተቃወመው የተበላሸ አስተዳደርን እንጂ ኢትዮጵያን አይደለም – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 1፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የኦሮሞ ሕዝብ በታሪኩ የተቃወመው የተበላሸ የአስተዳደር ሥርዓትን እንጂ ኢትዮጵያን አይደለም  አሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከኦቢኤን ጋር ባደረጉት ቆይታ ስለ ኦሮሞ ሕዝብ ጥያቄዎች እና ስለነበሩ ትግሎች የኢትዮጵያ ታሪክ እና የኦሮሞ ሕዝብ አበርክቶ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

በማብራሪያቸውም የኦሮሞ ሕዝብ ሀገርን በመገንባት ሂደትም ደሙን፣ አጥንቱን እና ላቡን ማፍሰሱን ገልጸዋል።

አፋን ኦሮሞን ከመናገር ባለፈ ባህልን፣ ማንነትን፣ ሥነ-ምግባርን (ሰፉ)፣ ታላላቆችን፣ ፍጥረታትን እና ፈጣሪን ማክበርን በውስጡ ያካተተ ጥልቅ ጥያቄ በኦሮሞ ህዝብ እንደሚነሳ አብራርተዋል።

በኦሮሞነት ማንነት አድጎ ቋንቋን መናገር ብቻውን የማንነት ጥያቄን ሙሉ በሙሉ እንደማይመልስ ገልጸው፤ የቋንቋ፣ የባህል እና የማንነት ጥያቄዎች አሁንም በቂ ምላሽ እንዳላገኙ አስገንዝበዋል።

ከዴሞክራሲ ጥያቄ አንጻር ደግሞ የኦሮሞ ሕዝብ የራሱ የሆነ አሳታፊ የገዳ ሥርዓት የነበረው ሕዝብ በመሆኑ፣ ራሱን በራሱ የማስተዳደር፣ የራሱን ሕግ የማውጣት እና በሕጉ የመተዳደር የረጅም ጊዜ ዴሞክራሲያዊ ጥያቄ ነበረው ብለዋል።

የመንግሥት አስተዳደር ደግሞ ሕዝቡ ከለመደው ዴሞክራሲያዊ አስተዳደር አንፃር ተቃራኒ ሲሆንበትም ጥያቄ ሲያነሣ መቆየቱን ተናግረዋል።

Exit mobile version