Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

አዲስ አበባን የጤና ቱሪዝም ማዕከል የማድረጉ ሥራ ተጠናክሮ ይቀጥላል – ከንቲባ አዳነች አቤቤ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 17፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) አዲስ አበባን የጤና ቱሪዝም ማዕከል የማድረጉ ሥራ ተጠናክሮ ይቀጥላል አሉ ከንቲባ አዳነች አቤቤ።

ከንቲባ አዳነች ኒው ሊፍ ሜዲካል ኮምፕሌክስ የተሰኘ የጤና ተቋምን በዛሬው ዕለት መርቀው ሥራ አስጀምረዋል።

ከንቲባዋ በዚህ ወቅት እንዳሉት÷ አዲስ አበባን የጤና ቱሪዝም ማዕከል እናደርጋታለን ስንል በመንግሥት ብቻ የምናሳካው ሳይሆን በግሉ ዘርፍ የሚገነቡትንም ታሳቢ በማድረግ ነው ብለዋል።

ለዚህም ዛሬ የተመረቀው ኒው ሊፍ ሜዲካል ሆስፒታል አንዱ ማሳያ መሆኑን ጠቁመው ÷ ተቋሙ ዘመኑን የዋጁ ቴክኖሎጂዎች የተሟሉለት ትልቅ የጤና ማዕከል መሆኑን አስረድተዋል፡፡

የጤና ዘርፍ ኢንቨስትመንት ከፍተኛ ወጪ የሚጠይቅ በመሆኑ በዘርፉ ለሚሰማሩ የጤና ተቋማትና ሆስፒታሎች አስፈላጊው ድጋፍ እንደሚደረግ አረጋግጠዋል፡፡

Exit mobile version