አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 1፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የብልጽግና ፓርቲ ም/ፕሬዚዳንት እና ዋና ጽ/ቤት ኃላፊ አደም ፋራህ በደቡብ ኮሪያ ሴኡል እየተካሄደ በሚገኘው የመጀመሪያው ዓለም አቀፍ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምክክር መድረክ ላይ እየተሳተፉ ነው።
ጉባዔው በዓለም አቀፍ ደረጃ በፖለቲካ ፓርቲዎች መካከል የጋራ ግንዛቤ ለመፍጠር እና ያላቸውን ትብብር ለማጠናከር ያለመ ነው፡፡
ከዛሬ ጀምሮ ለአራት ተከታታይ ቀናት በሚካሄደው ጉባዔ ላይ ከአፍሪካ፣ እስያ፣ አውሮፓ፣ ላቲን አሜሪካ እና ሰሜን አሜሪካ የተወጣጡ የፖለቲካ ፓርቲ መሪዎች ተሳትፈዋል፡፡
ጉባዔው በቀጣይ ቀናት በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ ይመክራል ተብሎ ይጠበቃል።

