አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 4፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኅብር ቀን በሀገር አቀፍ ደረጃ በተለያዩ ስፖርታዊ እና ማህበራዊ ሁነቶች እየተከበረ ይገኛል።
ዕለቱ በአዲስ አበባ ከተማ እና በተለያዩ ክልል ከተሞች በተለያዩ ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች ህብረተሰቡን በማሳተፍ እየተከበረ ይገኛል።
የስፖርት ዝግጅቶቹ አካላዊ ጤንነትን ከማጎልበት ባለፈ የህዝብ ለህዝብ ትስስርን ለማጠናከር፣ ሰላምን ለመስበክ እና በጋራ የልማት አላማዎች በአንድነት ለመቆም ትልቅ ምዕራፍ የሚፈጥሩ ናቸው።
በስፖርታዊ እንቅስቃሴው አመራሮች ፣ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች፣ ወጣቶች እና የዕድሜ ባለጸጋዎች በንቃት የተሳተፉበት ሲሆን፣ የጋራ ትብብርና መተሳሰብ ለሀገራዊ ግንባታ ያለውን ጠቀሜታ አጉልቶ አሳይቷል።

