አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 5፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ነገ መስከረም 1 ቀን 2019 ዓ.ም የሚከበረውን የአዲስ ዓመት በዓል ምክንያት በማድረግ 21 ጊዜ መድፍ ይተኮሳል አለ መከላከያ ሚኒስቴር።
በዚህ መሰረትም ነገ ከንጋቱ 12 ሰዓት ላይ 21 ጊዜ መድፍ የሚተኮስ መሆኑን የመከላከያ ሚኒስቴር ስፖርትና ኪነ ጥበባት ሥራዎች ማዕከል ለፋና ዲጂታል ገልጿል፡፡
ስለሆነም የመዲናዋ ነዋሪዎች በጉዳዩ ላይ ተገቢው መረጃ እንዲኖራቸው ሲል የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ አስታውቋል፡፡

