Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

አቶ ክርስቲያን ታደለን ጨምሮ ከ600 በላይ እስረኞች ከእስር ተፈቱ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 5፣ 2018 ዓ.ም (ኤፍ ኤም ሲ) አቶ ክርስቲያን ታደለን ጨምሮ ከ600 በላይ እስረኞች በይቅርታና ክሳቸው ተቋርጦ ከእስር ተፈትተዋል፡፡

ህገ መንግስታዊ ስርዓቱን በሀይል ለመናድ ሞክረዋል በሚል ታስረው የነበሩ ግለሰቦች እንዲፈቱ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ከመንግስት ጋር ላለፉት 5 ወራት ጥረት ሲያደርግ መቆየቱን አስታውቋል።

በፍርድ ቤት ውሳኔ ታሰረው የነበሩት በይቅርታ፣ በክስ ሂደት ላይ የነበሩት ደግሞ ክሱ እንዲቋረጥ ተደርጎ ከ6 መቶ በላይ እስረኞች በዛሬው እለት እንዲፈቱ መደረጉን የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽነር ብርሃኑ አዴሎ ገልጸዋል።

ይህ ቁጥር ክልሎች በየራሳቸው ከሚፈቷቸው ውጭ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን፣ የተፈቱት እስረኞች ከአማራና ከኦሮሚያ በፌደራል ደረጃ የታሰሩ እንደነበሩም ተመላክቷል፡፡

በግዛቸው ግርማዬ

Exit mobile version