Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

2ኛው ታላቁ የኢሬቻ ሩጫ ውድድር በቢሾፍቱ ይካሄዳል

አዲስ አበባ፣ መስከረም 8፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) ሁለተኛው የኢሬቻ የጎዳና ላይ ሩጫ ውድድር የፊታችን መስከረም 21 ቀን 2019 ዓ.ም በቢሾፍቱ ከተማ ይካሄዳል።

የኦሮሚያ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ ሮዛ ቢያ በሰጡት መግለጫ ÷ ውድድሩ የሕዝብ ስፖርት እና ባህል ማብሰሪያ መሆኑን ተናግረዋል።

10 ኪሎ ሜትር ርቀት በሚሸፍነው የኢሬቻ ሩጫ ውድድሩ ከ50 ሺህ በላይ ሰዎች እንደሚሳተፉ ይጠበቃል፡፡

በውድድሩ ላይ ታዋቂ አትሌቶችና የአትሌቲክስ ክለቦች እንደሚሳተፉ ጠቅሰው ÷ ለተሳታፊዎች የገንዘብ ሽልማት መዘጋጀቱን አመልክተዋል።

የቢሾፍቱ ከተማ ከንቲባ አለማየሁ አሰፋ በበኩላቸው÷ የከተማ አስተዳደሩ ውድድሩን በስኬት ማካሄድ የሚያስችል ዝግጅት ማድረጉን ተናግረዋል።

በሌላ በኩል አትሌት ጥሩነሽ ዲባባን ጨምሮ የዲባባ ቤተሰብ አባላት የውድድሩ አምባሳደር ተደርገው መመረጣቸው ተጠቁሟል፡፡

በሲፈን መኮንን

Exit mobile version