Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ በ81ኛው የተባበሩት መንግሥታት ጠቅላላ ጉባኤ ላይ እየተሳተፉ ነው

አዲስ አበባ፣ መስከረም 12፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) በፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ የተመራ ከፍተኛ ልዑክ ቡድን በኒውዮርክ እየተካሄደ በሚገኘው 81ኛው የተባበሩት መንግሥታት ጠቅላላ ጉባኤ ላይ እየተሳተፈ ይገኛል።

ጉባኤው “እምነትን መመለስ፣ ለውጥን መምራት፤ ለሁሉም የሚሰራ የተባበሩት መንግሥታት” በሚል መሪ ሐሳብ እየተካሄደ ይገኛል፡፡

በጉባኤው ላይ የፕላንና ልማት ሚኒስትር ፍፁም አሰፋ (ዶ/ር)፣ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምሥራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር ጌታቸው ረዳ እንዲሁም ከተለያዩ ተቋማት የተውጣጡ ተወካዮች ተገኝተዋል።

በዚህ መድረክ ኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅሟን እንዲሁም የአፍሪካን ጥቅም በሚመለከቱ ጉዳዮች ላይ ንቁ ተሳትፎ እንደምታደርግ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አመልክቷል፡፡

ልዑኩ ከዋናው ጉባኤ ጎን ለጎን በርካታ የሁለትዮሽና የባለብዙ ወገን ውይይቶችን እንደሚያደርግም ነው የተገለጸው፡፡

Exit mobile version