Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

አውስትራሊያ በኦፕን ኤአይ የሰው ሰራሽ አስተውሎት ድርጅት ላይ ምርመራ ጀመረች

አዲስ አበባ፣ መስከረም 14፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) አውስትራሊያ ኦፕን ኤአይ የተሰኘው የሰው ሰራሽ አስተውሎት ድርጅት የጤና ስርዓት መረጃዎቼን መዝብሯል በሚል ምርመራ ጀምራለች።
የአውስትራሊያ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ሪቻርድ ማርልስ ፥ የጤና ስርዓታችን መረጃ በጥበቃ ስር የነበረ ቢሆንም የኤአይ ኤጀንቶች ግን አጥሩን በመጣስ ሚስጥራዊ መረጃዎቻችንን መዝብረዋል ሲሉ ስለጉዳዩ ተናግረዋል።
የሳይበር ባለሙያዎች በበኩላቸው በጉዳዩ ላይ ባደረጉት የመጀመሪያ ግምገማ ተመዝብረዋል የተባሉት መረጃዎች በጥብቅ የደህንነት ማዕቀፍ ውስጥ እንዳልነበሩ አስረድተዋል።
ይሁን እንጂ ዋናው አሳሳቢ ጉዳይ የመረጃው መጠበቅ ወይም አለመጠበቅ ሳይሆን የኤአይ ኤጀንቶች የተፈቀደላቸውን ህጎችና ደንቦች ጥሰው በራሳቸው ፍላጎት የመረጃ መረብን በመጣስ የፈጸሙት የደህንነት ጥሰት መሆኑ ተመላክቷል።
በተለይም መረጃው በመንግስት ቁጥጥር ስር ያለ መሆኑ ደግሞ ጉዳዩን የበለጠ አሳሳቢ እንደሚያደርገው ቢቢሲ ዘግቧል።
የኦፕን ኤአይ ኩባንያ በበኩሉ የኤአይ ኤጀንቶቻችን እኛ ያላቀድነውን ርምጃ ወስደዋል ነገር ግን የሕመምተኞች ግላዊ መረጃ መወሰዱን የሚያሳይ ምንም አይነት መረጃ አላገኘሁም ሲል ምላሽ ሰጥቷል።
በእመቤት ሲሳይ
Exit mobile version