Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የአፍሪካን የወደፊት እጣ ፈንታ በጋራ ልንገነባው የተገባ ኃላፊነታችን ነው – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፣ መስከረም 20፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የአፍሪካን የወደፊት እጣ ፈንታ በጋራ ልንገነባው የተገባ ኃላፊነታችን ነው አሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) በኬንያ የላሙ የነዳጅ ማጣሪያ ፕሮጀክት ግንባታ ማስጀመሪያ ሥነ ሥርዓት ላይ ተሳትፈዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ÷የላሙ የነዳጅ ማጣሪያ ፋብሪካ የመሰረተ ድንጋይ የማስቀመጥ ሥነ ሥርዓት የአፍሪካን የኢንዱስትሪ አቅም ለማሳደግ ከፍተኛ ሚና እንዳለው አስገንዝበዋል፡፡
በተጨማሪም መጠነ ሰፊ እድሎችን ለመፍጠር እና በመላው ምስራቅ አፍሪካ ለላቀ ኢኮኖሚያዊና የኢንዱስትሪ ሉዓላዊነትን መሰረት ለመጣል ትልቅ ርምጃ መሆኑን የሚያረጋግጥ ሁነት ነው ብለዋል።
‎
‎በአህጉራችን የምትገኙ የኢንዱስትሪ መሪዎች፣ ባለሃብቶችና ስራ ፈጣሪዎች በአፍሪካ ላይ ኢንቨስት ልታደርጉ፣ ባለን አቅምና የጋራ ጸጋ እምነት ሊኖራችሁ እንዲሁም አህጉራዊ መፃኢ እድላችንን የሚወስኑ ለውጥ አምጪ ፕሮጀክቶችን ልትገነቡ ይገባል ነው ያሉት፡፡
‎
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) የአፍሪካን የወደፊት እጣ ፈንታ በጋራ ልንገነባው የተገባ ኃላፊነታችን ነው ሲሉም አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡
Exit mobile version