አዲስ አበባ፣ መስከረም 26፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የጅቡቲ ፕሬዚዳንት ኢስማኤል ኦማር ጊሌ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በድጋሚ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው በመሰየማቸው የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት አስተላልፈዋል።
ፕሬዚዳንቱ በመልዕክታቸው÷ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በድጋሚ የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው በመሰየምዎ እንኳን ደስ አለዎት ብለዋል፡፡
በሁለቱ ወንድማማች ሀገራት መካከል ያለውን ወዳጅነትና አጋርነት ይበልጥ ለማጠናከር ቁርጠኛ መሆናቸውንም አረጋግጠዋል፡፡

