Fana: At a Speed of Life!

የጅቡቲ ፕሬዚዳንት ኢስማኤል ኦማር ጊሌ ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት አስተላለፉ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 26፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የጅቡቲ ፕሬዚዳንት ኢስማኤል ኦማር ጊሌ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በድጋሚ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው በመሰየማቸው የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት አስተላልፈዋል።

ፕሬዚዳንቱ በመልዕክታቸው÷ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በድጋሚ የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው በመሰየምዎ እንኳን ደስ አለዎት ብለዋል፡፡

በሁለቱ ወንድማማች ሀገራት መካከል ያለውን ወዳጅነትና አጋርነት ይበልጥ ለማጠናከር ቁርጠኛ መሆናቸውንም አረጋግጠዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.