አዲስ አበባ፣ መስከረም 27፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከናይጄሪያ ምክትል ፕሬዚዳንት ካሺም ሼቲማ ጋር ተወያይተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት፤ በኢትዮጵያ ለሦስት ቀናት የሥራ ጉብኝት እና የላቀ አመራር ልምድ ልውውጥ ላይ የሚሳተፈውን ልዑክ ከመሩት የናይጄሪያ ምክትል ፕሬዚዳንት ካሺም ሼቲማ ጋር መወያየታቸውን ገልጸዋል።
ኢትዮጵያና ናይጄሪያ የበርካታ ብሔረሰቦች፣ የብዙ ባህሎች እና የከፍተኛ ሕዝብ ቁጥር ባለቤት የሆኑ ሀገራት ናቸው ሲሉም አስረድተዋል።
ይህም የሁለቱን ሀገራት ትብብር አጠናክረን ለማስቀጠልና የእርስ በእርስ የልምድ ልውውጥ ለማድረግ መልካም ዕድል ይሰጠናል ብለዋል።

