አዲስ አበባ፣ መስከረም 29፣2019 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከህንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሱብራህማንያም ጃይሻንካር ጋር ተወያይተዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው÷ የሕንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሱብራህማንያም ጃይሻንካር (ዶ/ር) እና ልዑካቸውን ዛሬ አግኝቻለሁ ብለዋል።
በውይይታቸው በኢትዮጵያ እና በሕንድ መካከል ያለውን ጠንካራና የቆየ ወዳጅነት የበለጠ ለማጠናከር ያለመ ምክክር ማድረጋቸውን ገልፀዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ከሰሞኑ በሕንድ ካደረጉት ጉብኝት እና ከጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ ጋር የነበራቸውን ቆይታ ተከትሎ በተጠናከረ ትብብርና በስትራቴጂካዊ አጋርነት ላይ የተመሰረተ ወዳጅነታችንን ይበልጥ ማሳደግ በሚቻልባቸው ዕድሎች ላይ መነጋገራቸውንም ጠቁመዋል።

