በትግራይ ክልል ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ታጣቂዎች ትጥቃቸውን በአቅራቢያቸው ለሚገኝ መከላከያ ሠራዊት በማስረከብ ወደ ተዘጋጁ የተሃድሶ ማዕከላት እንዲገቡ የብሔራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን ጥሪ አቅርቧል፡፡
በዚህም መሰረት ለታጣቂዎች የተዘጋጁ የተሃድሶ ማዕከላት የሚገኙባቸው አካባቢዎች የሚከተሉት ናቸው፡፡

በምስራቃዊ ዞን ዓዲግራት አካባቢ ያሉ – በዓዲግራት እና ውቅሮ ከተሞች

በማዕከላዊ ዞን አክሱም፣ ዓድዋ፣ ዓብዪዓዲን ጨምሮ የሚገኙ – በዓድዋ፣ አክሱም እና ዓብዪዓዲ ከተሞች

በሰሜን ምዕራብ ዞን ያሉ ታጣቂዎች – ሽረ ከተማ በሚገኘው የቀድሞ ማዕከላዊ እዝ ጠቅላይ መምሪያ ሪፖርት ማድረግ ይችላሉ፡፡