በትግራይ ክልል ሲንቀሳቀሱ ለነበሩ ታጣቂዎች የተዘጋጁ የተሃድሶ ማዕከላት የሚገኙባቸው አካባቢዎች On Oct 10, 2026 52 በትግራይ ክልል ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ታጣቂዎች ትጥቃቸውን በአቅራቢያቸው ለሚገኝ መከላከያ ሠራዊት በማስረከብ ወደ ተዘጋጁ የተሃድሶ ማዕከላት እንዲገቡ የብሔራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን ጥሪ አቅርቧል፡፡ በዚህም መሰረት ለታጣቂዎች የተዘጋጁ የተሃድሶ ማዕከላት የሚገኙባቸው አካባቢዎች የሚከተሉት ናቸው፡፡ በደቡባዊ ዞን ያሉ የቀድሞ ታጣቂዎችና አመራሮች – በማይጨው እና መኾኒ ከተሞች በደቡብ ምስራቅ ዞን መቐለን ጨምሮ ያሉ – በመቐለ ከተማ በሚገኘው የሰሜን ዕዝ ጠቅላይ መምሪያ በምስራቃዊ ዞን ዓዲግራት አካባቢ ያሉ – በዓዲግራት እና ውቅሮ ከተሞች በማዕከላዊ ዞን አክሱም፣ ዓድዋ፣ ዓብዪዓዲን ጨምሮ የሚገኙ – በዓድዋ፣ አክሱም እና ዓብዪዓዲ ከተሞች በሰሜን ምዕራብ ዞን ያሉ ታጣቂዎች – ሽረ ከተማ በሚገኘው የቀድሞ ማዕከላዊ እዝ ጠቅላይ መምሪያ ሪፖርት ማድረግ ይችላሉ፡፡ 52 Share FacebookTwitterTelegramWhatsAppEmailViberPrint