አዲስ አበባ፣ ሕዳር 7፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያ የምታስተናግደው ኮፕ32 ብሔራዊ ጥረቶቻችንን ወደ ዘላቂ ውጤት ለመለወጥ ትልቅ ዕድል ይፈጥራል አሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)፡፡
የኮፕ32 ብሔራዊ አስተባባሪ ኮሚቴ አጠቃላይ የሥራ ሂደት ግምገማ በዛሬው ዕለት ተካሂዷል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት፤ ብሔራዊ አስተባባሪ ኮሚቴውን በመሰብሰብ አጠቃላይ የሥራ ሂደቱን ገምግመናል ብለዋል፡፡
በግምገማው ላይ ዝግጅቶችን ከፈትሽን በኋላ ሥራዎች የሚመሩበት ስትራቴጂያዊ አቅጣጫ ሰጥቻለሁ ነው ያሉት፡፡
ጉባኤውን በስኬት ለማስተናገድ ሁሉም ግብረ ኃይሎች ተናብበው እንዲሠሩ በማድረግ የተቀናጀ ሁሉን አቀፍ የመንግሥት አካሄድ መከተል ወሳኝ መሆኑን በአጽንኦት ማሳሰባቸውን ገልጸዋል፡፡
ኮፕ32 ታላቅ ዓለም አቀፍ ጉባኤ ከመሆኑ ባለፈ የኢትዮጵያን የአየር ንብረትና የአካባቢ ጥበቃ አጀንዳን ለማራመድ፣ አጋርነትን ለማጠናከር፣ ኢንቨስትመንትን ለመሳብ እንዲሁም ብሔራዊ ጥረቶቻችንን ወደ ዘላቂ ውጤት ለመለወጥ ትልቅ ዕድል ይፈጥራል ብለዋል።
#ኢትዮጵያ #ኮፕ_32_ኢትዮጵያ #COP31 #COP32 #COP32ETHIOPIA #fanamediacorporation

