አዲስ አበባ፣ ሕዳር 7፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ በጊዜያዊነት አቋርጦት የነበረውን ወደ ሽረ ከተማ የሚያደርገውን መደበኛ በረራ ከሕዳር 8 ቀን 2019 ዓ.ም ጀምሮ እንደገና እንደሚያስጀምር አስታውቋል።
የአየር መንገዱ ደንበኞች የጉዞ ትኬት ለማስያዝ በአቅራቢያቸው ወደሚገኘው የአየር መንገዱ ቢሮ በመሄድ ወይም በ6787 የጥሪ ማዕከል በመደወል አገልግሎቱን መጠቀም እንደሚችሉ አሳውቋል።

