የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ሽረ ከተማ የሚያደርገውን መደበኛ በረራ እንደገና ሊጀምር ነው
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 7፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ በጊዜያዊነት አቋርጦት የነበረውን ወደ ሽረ ከተማ የሚያደርገውን መደበኛ በረራ ከሕዳር 8 ቀን 2019 ዓ.ም ጀምሮ እንደገና እንደሚያስጀምር አስታውቋል።
የአየር መንገዱ ደንበኞች የጉዞ ትኬት ለማስያዝ በአቅራቢያቸው ወደሚገኘው የአየር መንገዱ ቢሮ በመሄድ ወይም በ6787 የጥሪ ማዕከል በመደወል አገልግሎቱን መጠቀም እንደሚችሉ አሳውቋል።