Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

5ኛው ዓለም አቀፍ የአፍሪካ የሕዝብ ጤና ጉባኤ በአዲስ አበባ መካሄድ ጀመረ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 14፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) 5ኛው ዓለም አቀፍ የአፍሪካ የሕዝብ ጤና ጉባኤ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት በአዲስ አበባ መካሄድ ጀምሯል፡፡

ጉባኤው “የአፍሪካ የጤና ደህንነት እና ሉዓላዊነት፤ ከጤና ጥገኝነትና ተጋላጭነት ወደ ባለቤትነትና ጽናት የሚደረግ ሽግግር” በሚል መሪ ሀሳብ ነው እየተካሄደ የሚገኘው፡፡

በጉባኤው ላይ የተለያዩ ሀገራት መሪዎች፣ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች፣ የሕዝብ ጤና ባለሙያዎች እንዲሁም ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች የአፍሪካን የወደፊት የጤና ራዕይ ወደፊት ለማራመድ ምድረ ቀደምት በሆነችው ኢትዮጵያ ተሰባስበዋል።

የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት መረጃ እንዳመለከተው፥ የአፍሪካ ዲፕሎማሲያዊ ዋና ከተማ የሆነችው አዲስ አበባ ጉባኤውን በማስተናገድ ዳግም የአፍሪካ የወደፊት ዕጣ ፈንታ ማዕከል ሆናለች፡፡

Exit mobile version