Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በመቐለ ከተማ የነዳጅ ማደያዎች ወደ መደበኛ ሥራ ተመለሱ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 15፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) በመቐለ ከተማ የሚገኙ የነዳጅ ማደያዎች ከዛሬ ጀምሮ ወደ መደበኛ አገልግሎት ተመልሰዋል።

የነዳጅ ማደያዎቹ ወደ መደበኛ ሥራ መመለሳቸው በከተማዋ ለሚገኙ የነዳጅ ተጠቃሚዎች የአቅርቦት ችግርን ለማቃለል እንደሚያግዝ ይጠበቃል።

እርምጃው በነዳጅ አቅርቦትና ስርጭት ሂደት ላይ የሚስተዋሉ ሕገወጥ አሠራሮችን ለመቆጣጠርና ለማስተካከልም አስተዋጽኦ ያደርጋል።

ተደራሽና የተረጋጋ የነዳጅ አቅርቦት ማረጋገጥ የነዋሪዎችን የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴ ከማቀላጠፍ ባለፈ የከተማዋን ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ ለማጠናከር ወሳኝ ሚና አለው።

በአሸናፊ ሽብሩ

Exit mobile version