Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በ24 ሰዓታት 1 ሺህ 206 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ሲገኝባቸው፤ የ21 ሰዎች ሕይወት አልፏል

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 1፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 25 ሺህ 158  የላብራቶሪ ምርመራ 1 ሺህ 206 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።

በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 58 ሺህ 672 መድረሱንም ሚኒስቴሩ ያወጣው እለታዊ መረጃ ያመለክታል።

ከዚህ ባለፈ የ21 ሰዎች ህይወት በቫይረሱ ምክንያት ያለፈ ሲሆን፥ በአጠቃላይ በኢትዮጵያ በቫይረሱ ምክንያት ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር 918 መድረሱንም አመላክተዋል።

በሌላ መልኩ በትናንትናው እለት 531 ሰዎች ከኮሮና ቫይረስ ያገገሙ ሲሆን፥ በአጠቃላይ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 21 ሺህ 307 መድረሱም ተገልጿል።

ከቫይረሱ ጋር በተያያዘ እስካሁን ለ1 ሚሊየን 44 ሺህ 0 ሰዎች ምርመራ የተደረገ ሲሆን፥ በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 58 ሺህ 672 ደርሷል።

አሁን ላይ ቫይረሱ ያለባቸው ሰዎች ቁጥር 36 ሺህ 445 ሲሆን፥ ከእነዚህም ውስጥ 308 ሰዎች በጽኑ የታመሙ መሆናቸውንም የጤና ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል።

እስካሁን በኢትዮጵያ 21 ሺህ 307 ሰዎች ከቫይረሱ ሲያገገሙ፤ የ918 ሰዎች ህይወት አልፏል፤ 2 ሰዎች ወደ ሀገራቸው መመለሳቸው ይታወሳል።

#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

Exit mobile version