አዲስ አበባ፣ ሕዳር 20፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) በትግራይ ክልል የሚንቀሳቀሱ 19 የፖለቲካ ፓርቲዎችን ያቀፈ የትግራይ ክልል የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት በይፋ ተመሥርቷል።
በምሥረታ መድረኩ ላይ የአምስት ፓርቲዎች አመራሮች የምክር ቤቱ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ሆነው ተመርጠዋል።
በዚህም መሠረት አቶ ዓምዶም ገብረሥላሴ ሰብሳቢ፣
አቶ ብርሃነ ገብረጻድቅ ምክትል ሰብሳቢ፣
አቶ ከበደ አሰፋ ደግሞ የምክር ቤቱ ጸሐፊ ሆነው ተመርጠዋል።
አቶ ሀፍቱ ኪሮስ እና አቶ ጉዕሽ ጊደይ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት ሆነው ተመርጠዋል።
በአሸናፊ ሽብሩ

