Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የብሔራዊ ደህንነት ምክር ቤት በወቅታዊ የደህንነትና ፀጥታ ጉዳዮች ላይ በመወያየት አቅጣጫዎችን አስቀመጠ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 4፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የብሔራዊ ደህንነት ምክር ቤት በሃገሪቱ ወቅታዊ የደህንነትና ፀጥታ ጉዳዮች ላይ ውይይት በማድረግ ቀጣይ አቅጣጫዎችን አስቀመጠ።
 
ምክር ቤቱ በሃገሪቱ የተቃጡ፣ የከሸፉ እና ጉዳት ያደረሱ የብሔራዊ ደህንነት ስጋቶችን በዝርዝር ዳስሷል።
 
በአሁኑ ወቅት ያሉ ወቅታዊ የደህንነት ጉዳዮችንም በዝርዝር የተመለከተ ሲሆን፥ በቀጣይ ስጋቶቹን በተቀናጀ መልኩ መግታት የሚቻልበት አግባብ ላይ መወያየቱን የጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት አስታውቋል።
 
በዚህም የሃገርን ሉዓላዊነት፣ የዜጎችን ሰላምና ደህንነት ለማስጠበቅና የህግ የበላይነትን ለማስከበር መንግስት በቁርጠኝነት እንደሚሰራ ተመልክቷል
 
ይህንንም እውን ለማድረግ መከላከያን ጨምሮ ሁሉም የደህንነትና ጸጥታ ተቋማት እስካሁን እያደረጉት ያለውን ጥረትና መስዋዕትነት አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ምክር ቤቱ አረጋግጧል።
Exit mobile version