አዲስ አበባ፣ መስከረም 2፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) የወረቀት አልባ ጉምሩክ አገልግሎት ምረቃ ስነ ሥርዓት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በተገኙበት በዛሬው ዕለት ተከናውኗል።
አገልግሎቱ ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ ደረጃ ያላት የንግድ ትስስር እንዲጠናከር፣ የጋራ የድንበር አስተዳደር ስርዓት በውጤታማነት እንዲከናወን፣ እንዲሁም በጉምሩክ እና በንግዱ ማህበረሰብ መካከል ጠንካራ ትብብር እንዲፈጠር ያስችላል ተብሏል።
ከዚያም ባለፈ የመረጃ አስተዳደርና ልውውጥ ስርዓትን በቴክኖሎጂ በመታገዝ ለማዘመን ይረዳልም ነው የተባለው።
በተጨማሪም በጉምሩክ ስርዓት ሂደት ተጠያቂነት እና ግልጸኝነትን በመፍጠር፣ የሰነድ መጭበርበርን በማስቀረት ፍትሐዊ የንግድ ሥርዓት እንዲሰፍን አስተዋጽኦ ያደርጋል መባሉን ከጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
#FBC
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

