Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በኦሮሚያ 1 ነጥብ 8 ሚሊየን ለሚሆኑ ተማሪዎች ድጋፍ ለማድረግ ገቢ እየተሰበሰበ መሆኑ ተገለፀ

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 18 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ)በ ኦሮሚያ 1 ነጥብ 8 ሚሊየን ለሚሆኑ ተማሪዎች ድጋፍ ለማድረግ ገቢ እየተሰበሰበ መሆኑ ተገለፀ።
“እኔ ለአንድ ተማሪ” በሚል መሪ ሃሳብ የኦሮሚያ ክልል ሴቶች፣ ህፃናትና ወጣቶች ቢሮ÷ የትምህርት ቁሳቁስ መግዛት ለማይችሉ 1 ነጥብ 8 ሚሊየን ለሚሆኑ ተማሪዎች ድጋፍ ለማድረግ የገቢ ማሰባሰብ ሥራውን እያከናወነ መሆኑን ገልጿል።
በዛሬው ዕለት የተጀመረው የገቢ ማሰባሰብ ሥራው ለአንድ ሳምንት የሚቆይ ነው ተብሏል።
ከኦሮሚያ የተለያዩ ቢሮዎች በአንድ ቀን ብቻ 4 ነጥብ 1 ሚሊየን ብር መሰብሰብ መቻሉም ነው የተገለጸው ።
የገቢ ማሰባሰብ ሂደቱ በክልል፣ በዞን፣ በወረዳ እና በቀበሌ እንደሚከናወን እና ዓመቱን በሙሉ ለተማሪዎች የቁሳቁስ ድጋፉ እንደሚደረግም ተነግሯል።
ከትምህርት ቁሳቁስ ባለፈም የኮቪድ-19 መከላከያ ድጋፍ እንደሚደረግላቸው መገለጹን ከትምህርት ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
#FBC
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።
Exit mobile version