Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ ሆረ ፊንፊኔ እና የሆረ አርሰዲ በዓል በሰላም እንዲጠናቀቅ አስተዋጽዖ ላደረጉ አካላት ምስጋና አቀረቡ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 24፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ)ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ሆረ ፊንፊኔ እና የሆረ አርሰዲ በዓል በሰላም እንዲጠናቀቅ አስተዋጽዖ ላደረጉ አካላት ምስጋና አቅርበዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዓሉ በሰላም እንዲጠናቀቅ አስተዋጽዖ ላደረጋችሁ አባገዳዎች፣ ሲንቄዎች ፣ወጣቶች ፣ርዕሳነ መስተዳድሮች ፣ የጸጥታ ተቋማት፣ አጠቃላይ የበዓሉ ታዳሚዎች እና ሚዲያዎች በዓሉ በሰላም ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅበት ሰዓት ድረስ ላደረጋችሁት አስተዋጽኦ ምስጋናዬን አቀርባለሁ ነው ያሉት።

እንዲሁም የሀገራችን ባህሎች እና እሴቶች መሠረቱ ሰላም ወዳድነት እና ተባባሪነት እንደመሆኑ ለአለም ህዝብ ከምናሳውቅባቸው መድረኮች ዋነኞቹ የአደባባይ በዓላት ናቸው ሲሉም ተናግረዋል፡፡

Exit mobile version