አዲስ አበባ ፣መስከረም 26 ፣2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የገበታ ለሀገር ፕሮጀክትን አስመልክቶ ለውጭ ሀገር ኢንቨስተሮች ገላፃና ማብራሪያ የተደረገላቸው ነው።
ለውጭ ሀገር ኢንቨስተሮች በገበታ ለሀገር ፕሮጀክት ተግባራዊ በሚደረጉት የወንጪ ፣ ጎርጎራ እና ጨበራ ጩርጩራ ፕሮጀክቶች ነው ገለፃ እየተደረገላቸው የሚገኘው።
በዚህም ስለፕሮጀክቶቹ አጠቃላይ ዝርዝር ፍላጎትና ተግባራዊነት የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስትሩ ዶክተር አብረሃም በላይ ፣ የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣም ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር ሀብታሙ ተገኝ እና የጎርጎራ ፕሮጀክት ስራ አስኪያጅ ዶክተር ፍሰሃ ተገኝ ገለጻ ተደርጎላቸዋል።
በገለጻውም ፕሮጀክቶቹ በውስጠቸው ስለሚይዟቸው ፣ ስላላቸው የቱሪስት መስህብ እና ተፈጥሮአዊ አቅም እንዲሁም ስለሚፈጥሩት የስራ እድል ተነስቷል።
ባለሃበቶቹም ለፕሮጀክቶቹ ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ ቀርቦላቸዋል።
በሀብታሙ ተ/ስላሴ
#FBC
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

