አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 1 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለግብርናው ዘርፍ የሚያስፈልጉ የቴክኖሎጂ አቅርቦት፣ የሥራ እድል ፈጠራ፣ የገበያ ትስስር እና የክላስተር ፋይናንስ ላይ በትኩረት እንደሚሰራ አስታወቁ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በአርሲ ዞን ዶዶታ እና ሄጦሳ ወረዳዎች የተሠሩ የግብርና ሥራዎችን ጎብኝተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከዓመት በፊት በአካባቢው ባደረጉት ጉብኝት በግብርናው ዘርፍ ያስቀመጧቸውን የሥራ አቅጣጫዎች አፈጻጸም ለማየት መገኘታቸውም ነው የተገለጸው።
በዚህም በእርሻ አያያዝና እና የግብርና ሁኔታው እንዳስደሰታቸውና ቀጣይ ሥራዎችም እንደሚያስፈልጉ መናገራቸውን ኢቢሲ ዘግቧል።
በጉብኝታቸው ወቅት ከተከሰተው የአንበጣ ወረርሽኝ ጋር በተያያዘ ለአንበጣ መከላከያ ኬሚካል ርጭት የሚውሉ 10 አውሮፕላኖችን በኪራይ ለማምጣት እየተሠራ እንደሚገኝም ገልጸዋል።

