Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ኢትዮጵያ እና የዓለም ባንክ የ400 ሚሊየን ዶላር የድጋፍ ስምምነት ተፈራረሙ

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 4 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ እና የዓለም ባንክ የ400 ሚሊየን ዶላር የድጋፍ ስምምነት ተፈራረሙ፡፡

ስምምነቱን የኢፌዴሪ የገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሽዴ እና በኢትዮጵያ፣ ኤርትራ፣ ደቡብ ሱዳን እና ሱዳን የዓለም ባንክ ዳይሬክተር ኦስማን ዲዮን ተፈራርመውታል፡፡

ድጋፉ በመላ ሃገሪቱ በሚገኙ 83 ከተሞች ለከተማ ሴፍቲኔት እና ለወጣቶች የስራ እድል ፈጠራ ይውላል ተብሏል፡፡

በከተሞች በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ ነዋሪዎችን ህይዎት ለማሻሻል የሚውል ሲሆን 816 ሺህ ሰዎችም ተጠቃሚ ይሆናሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

የዓለም ባንክ ባለፈው መስከረም 22 ቀን 2013 ዓ.ም የ400 ሚሊየን ዶላሩን ድጋፍ ማፅደቁ ይታወሳል፡፡

Exit mobile version