Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የተመድ የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን በኢትዮጵያ አሁናዊ ሁኔታ ላይ የሚለቀቁ ሀሰተኛ መረጃዎች ላይ ጥንቃቄ ሊደረግ እንደሚገባ አሳሰበ

አዲስ አበባ ፣ህዳር 3 ፣2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ )የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስደተኞች ጉዳይ ከፍተኛ ኮሚሽን በኢትዮጵያ አሁናዊ ሁኔታ ላይ የሚለቀቁ ሀሰተኛ መረጃዎች ላይ ጥንቃቄ ሊደረግ እንደሚገባ አሳሰበ ።
ድርጅቱ አያይዞም ሱዳን በሚገኘው የኮሚሽኑ ህጋዊ የቲዊተር ገጽ እንደተለጠፈ ተደርጎ የቀረበው ምስል ሀሰተኛ ነውም ሲል አስታውቋል።
በዚህም በኢትዮጵያ እና በሱዳን አሁናዊ ሁኔታ ላይ የሚለቀቁ ሀሰተኛ መረጃዎች ላይ ጥንቃቄ ሊደረግ እንደሚገባ አስጠንቅቋል።
በመሆኑም ድርጅቱ በማኅበራዊ የትስስር ድረ ገጾች ላይ መረጃዎችና ምስሎችን ከማውጣትና ከማጋራት በፊት ማረጋገጥ፣ ሀላፊነት መውሰድና ጥንቃቄ ማድረግ ይገባልም ነው ያለው።
#FBC
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።
Exit mobile version