Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

አቶ ደመቀ መኮንን ከጀርመን መራሄተ መንግስት የውጭና ደህንነት ፖሊሲ አማካሪ ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 18፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ከጀርመን መራሄተ መንግስት የውጭና ደህንነት ፖሊሲ አማካሪ ዶክተር ጃን ሄከር ጋር ተወያዩ።

በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን የተመራው የኢትዮጵያ መንግስት ከፍተኛ ልኡክ ጀርመን በርሊን ይገኛል።

በቆይታቸውም ከጀርመን መራሄተ መንግስት የውጭና ደህንነት ፖሊሲ አማካሪ ዶክተር ጃን ሄከር ጋር ተወያይተዋል።

በውይይቱ ወቅትም ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ አቶ ደመቀ የኢትዮጵያን ወቅታዊ ሁኔታ አስመልክተው ገለፃ አድርገዋል።

በዋናነት በትግራይ ክልል የተጀመረውን ህግ የማስከበር ዘመቻ አስመልክቶ የመንግሥትን አቋም ግልፅ አድርገዋል።

መንግሥት በሀገሪቱ የውስጥ ጉዳይ ዙሪያ የጀመረው ህግ የማስከበር እርምጃ ወንጀለኞችን ለህግ የማቅረብ ዓላማ እንዳለው አብራርተዋል።

በህግ ማስከበር ሂደት ለዓለም አቀፍ የሰብዓዊ ድጋፍ ሰጪ አካላት ለአገልግሎት ምቹ እና ነፃ መንቀሳቀሻ ኮሪደር መመቻቸቱን ገልፀዋል።

የተጀመረው ህግ የማስከበር ዘመቻ በፍጥነት እንደሚጠናቀቅ ለአማካሪው ማረጋገጣቸውን ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

Exit mobile version