Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በህዳሴ ግድቡ ዙሪያ በአፍሪካ ህብረት አደራዳሪነት የተጀመረው ውይይት እንዲቀጥል ስምምነት ተደረሰ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 7፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በአፍሪካ ህብረት አደራዳሪነት የተጀመረው የታላቁ የህዳሴ ግድብ የሦስትዮሽ ድርድር እንዲቀጥል ስምምነት ላይ መደረሱ ተገለጸ፡፡

የውሃ፣ የመስኖና ኢኒርጂ ሚኒስትር ዶክተር ስለሺ በቀለ ከሱዳን የመስኖና የውሃ ሚኒስትር ፕሮፌሰር ያሲር አባስ ጋር ተወያይተዋል፡፡

ሁለቱ ሚኒስትሮች በሦስትዮሹ የድርድር ሂደት ላይ መወያየታቸው የተጠቀሰ ሲሆን ድርድሩ እንዲቀጥል መወሰናቸው ነው የተሰማው፡፡

እንዲሁም የአፍሪካ ህብረት የባለሙያዎች ቡድን በድርድሩ ሂደት ላይ ትልቅ ሚና እንዲኖረው ስምምነት ላይ መደረሱ ተገልጿል፡፡

የውሃ፣ የመስኖና ኢኒርጂ ሚኒስትር ዶክተር ስለሺ በቀለ ከሱዳን ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሃምዶክ ጋርም ውይይት ማድረጋቸውን የሀገሪቱ መገናኛ ብዙኀን ዘግበዋል፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version