አዲስ አበባ፣ታህሳስ 13፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን የተመራው ልዑክ ከሱዳን
ሉዐላዊ ም/ቤት እና የሽግግር ወታደራዊ ም/ቤት ምክትል ሊቀ መንበር ሌተናንት ጄኔራል መሐመድ ሐምዳን ዳጋሎ ጋር ተወያየ።
በሱዳን ካርቱም በተካሄደው ሁለተኛው የኢትዮ- ሱዳን የድንበር ጉዳዮች የከፍተኛ አመራር የፖለቲካ ውይይት ላይ የተሳተፈው የኢትዮጵያ ልዑክ ከሱዳን ሉዐላዊ ም/ቤት እና የሽግግር ወታደራዊ ም/ቤት ምክትል ሊቀ መንበር ሌተናንት ጄኔራል መሐመድ ሐምዳን ዳጋሎ ጋር ተወያይቷል።
ልዑኩን የመሩት አቶ ደመቀ መኮንን ሲሆኑ በውይይቱም የሁለቱን ሀገራት ትብብርና ግንኙነት ማጠናከር በሚቻልባቸው ርዕሶች ላይ መክረዋል።
በተጨማሪም ወቅታዊ የሁለቱ ሀገራት ጉዳዮች እና አከባቢያው ሰላም ላይ ተወያይተዋል።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

