Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

6ኛው ሀገር አቀፍ ምርጫ ግንቦት 28 ቀን 2013 ዓ.ም እንዲሆን ሃሳብ ቀረበ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 16፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በተያዘው ዓመት የሚካሄደው 6ኛው ሀገር አቀፍ ምርጫ የድምፅ መስጫ ቀን ግንቦት 28 ቀን 2013 ዓ.ም እንዲሆን ሀሳብ ቀረበ።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ከፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር የምርጫ ረቂቅ የጊዜ ሰሌዳን አስመልክቶ የምክክር መድረክ እያካሄደ ነው።
በዚህ ወቅትም የምርጫው አጠቃላይ ዉጤትም ከግንቦት 29 እስከ ሰኔ 21 ባሉት ቀናት በቦርዱ ይፋ እንደሚደረግ ተጠቁሟል።
ቦርዱ ስድተኛውን ሀገር አቀፍ ምርጫ አስመልክቶ ዋና ዋና ተግባራት የሚከናወኑበትን የጊዜ ሰሌዳ ይፋ አድርጓል።
በዚህም መሰረት ከታህሳስ 16 እስከ ጥር 16 ቀን 2013 የምርጫ ክልል ቢሮዎች መከፈት፣ ከጥር 24 እስከ የካቲት 21 ቀን 2013 ለምርጫ አስፈጻሚዎች ስልጠና – ለመራጮች ምዝገባ፣ ከጥር 17 እስከ የካቲት 21 ቀን 2013 የመራጮች ትምህርት ለእጮዎች ምዝገባ፣ ከጥር 22 እስከ የካቲት 06 ቀን 2013 ፓርቲዎች የምርጫ ምልክት ማስገቢያ እና መወሰኛ፣ የካቲት 08 እስከ የካቲት 21 ቀን 2013 የእጩዎች ምዝገባ፣የካቲት 08 እስከ ግንቦት 23 ቀን 2013 የምረጡኝ ቅስቀሳ / የምርጫ ዘመቻ፣ ከጥር 24 እስከ ሚያዝያ 1 ቀን 2013/የመራጮች ትምህርት – ለመራጮች ምዝገባ፣የካቲት 3 ቀን 2013 የምርጫ ጣቢያዎች ዝርዝር ይፋ ማድረጊያ በመሆን ሃሳብ ቀርቧል፡፡
ከየካቲት 22 እስከ መጋቢት 21 ቀን 2013 ምራጮች ምዝገባ፣ ከመጋቢት 22 እስከ ሚያዝያ 01 ቀን 2013 የመራጮች ምዝገብ ይፋ ማድረጊያ ጊዜ ፣ከመጋቢት 19 እስከ መጋቢት 21 ቀን 2013 የድምጽ መስጫ ወረቀት ቅደም ተከተል ሎተሪ፣ ከመጋቢት 22 እስከ መጋቢት 23 ቀን 2013 የእጩዎች ዝርዝር ይፋ ማድረጊያ፣ ከመጋቢት 21 እስከ ግንቦት 10 ቀን 2013 የድምጽ መስጫ ወረቀት ህትመት፣ከሚያዝያ 16 እስከ ሰኔ 3 ቀን 2013 የመራጮች ትምህርት – ለድምጽ መስጫ ቀን፣ከግንቦት 24 እስከ ግንቦት 27 ቀን 2013 ቅስቀሳ ማድረግ የማይቻልበት የጥሞና ጊዜ፣ ግንቦት 28 ቀን 2013 በምርጫ ጣቢያ ደረጃ ውጤት የሚገለጽበት ፣ ግንቦት 28 የድምፅ መስጫ ቀን ፣ግንቦት 28 የደቡብ ምእራብ ህዝበ ውሳኔ ድምፅ መስጫ ቀን፣ሰኔ 5 ቀን 2013 ለአዲስ አበባ እና ለድሬዳዋ ከተማ አስተዳደሮች ድምፅ መስጫ ቀን፡፡
ከግንቦት 20 እስከ 29 ቀን 2013 ዓ.ም በምርጫ ጣቢያ ደረጃ ውጤት የሚገለፅበት ይሆናል ተብሏል።
በአላዛር ታደለ
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፦
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!በአላዛር ታደለበአላዛር ታደለ
Exit mobile version