አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 20 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ህብረተሰቡ የአፍ እና የአፍንጫ መሸፈኛ ጭምብሎችን በአግባቡ በመጠቀም የጤና ባለሙያዎችን እንዲያግዝ ጥሪ አቀረቡ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በፌስ ቡክ ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት የኮቪድ-19 ታማሚዎች ቁጥር በማሻቀብ ላይ መሆኑን አስታውቀዋል።
አሁን ላይም የጽኑ ሕሙማን ክፍል ያለውን ዐቅም ሁሉ አሟጦ እየሠራ እንደሚገኝ ጠቅሰው፥ በዚህ ወቅት የጥንቃቄ እርምጃዎችን ቸል ማለት እንደማይገባም አንስተዋል፡፡
ከዚህ አንጻርም ህብረተሰቡ የራሱን ሕይወት እንዲታደግ የሌሎችንም ሕይወት እንዲያተርፍም ጥሪ አቅርበዋል፡፡
የአፍ እና የአፍንጫ መሸፈኛ ጭምብሎችን በአግባቡ በመጠቀምም የጤና ባለሙያዎችን እናግዝም ብለዋል በመልዕክታቸው፡፡
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

