Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ለፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ የታንዛኒያው ፕሬዘዳንት ጆሴፍ ማጉፉሊ አቀበባል አደረጉላቸው

አዲስ አበባ ፣ ጥር 17፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ታንዛኒያ ሲገቡ የሀገሪቱ ፕሬዘዳንት ጆሴፍ ማጉፉሊ አቀበባል አደረጉላቸው።

ፕሬዚዳንቷ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ነው ወደ ታንዛንያ ያቀኑት።

በዚህ ወቅት ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ለፕሬዚዳንት ጆሴፍ ማጉፉሊ የኢትዮጵያን ባህላዊ ልብስ በስጦታ አበርክተውላቸዋል።

በታንዛንያ ቆይታቸው የናይል ቤዚን ኮሚሽንን ለማቋቋም በሚያስችሉ ጉዳዮች ዙሪያ ከፕሬዚዳንት ጆሴፍ ማጉፉሊ ጋር ይመክራሉ ተብሎ ይጠበቃል

ከአባይ ተፋሰስ ሀገራት መካከል ታንዛንያ የአባይ ውሃን በጋራ መጠቀም የሚያስችለውን የትብብር ማዕቀፍ ስምምነትን ቀድማ የፈረመች ሀገር መሆኗ ይታወሳል፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version