Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የአስር ዓመት የልማት እቅድ በሁሉም ዘርፍ ስኬታማ እንዲሆን የትራንስፖርት ዘርፉን በቀዳሚነት ማዘመን ያስፈልጋል-  አቶ ደመቀ መኮንን

አዲስ አበባ ፣ ጥር 18፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ የጀመረችው የአስር አመት የልማት እቅድ በሁሉም ዘርፍ ስኬታማ እንዲሆን የትራንስፖርት ዘርፉን በቀዳሚነት ማዘመን እንደሚገባ ምክትል ጠቅላይ ሚንስትርና የውጭ ጉዳይ ሚንስትሩ አቶ  ደመቀ መኮንን ተናገሩ።

የትራንስፖርት ዘርፉ የአስር አመታት መሪ እቅድ በርካታ ባለድርሻ አካላት በተገኙበት ውይይት ተደርጎል::

በውይይቱ ላይ የተገኙት አቶ ደመቀ መኮንን፣ ሁሉም የሀገሪቱ የምጣኔ ሀብት እንቅስቃሴ በትራንስፖርት ዘርፋ ላይ ጥገኛ በመሆኑ በትኩረት ሊሰራበት ይገባል ብለዋል።

ለዚህ ስኬት መንግስት እቅዱን ከማዘጋጀት ጀምሮ ከፍተኛ በጀት በመመደብ በትኩረት እንደሚሰራ አስረድተዋል።

የትራንስፖርት ሚንስትሯ  ወ/ሮ ዳግማዊት ሞገስ በበኩላቸው፣ በአስር አመቱ የትራንስፖርት መሪ እቅድ ቴክኖሎጂን መሠረት ያደረገ የትራንስፖርት ስርዓት ለመዘርጋት በስፋት ይሰራል ሲሉ ገልጸዋል።

በተለይ ደግሞ የትራፊክ አደጋን ትርጉም ባለው መልኩ ለመቀነስ እንደሚሰራም ሚኒስትሯ መናገራቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

 

Exit mobile version