አዲስ አበባ ፣ ጥር 19፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በክልሉ 125ኛውን የዓድዋ የድል በዓል ለማክበር ዝግጅት መጀመሩን የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት አስታወቀ፡፡
በኦሮሚያ ክልል በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የማኅበራዊ ዘርፍ አስተባባሪ አቶ አዲሱ አረጋ እንዳስታወቁት ዓድዋ የመላዉ ጥቁር ህዝቦች ኩራት ነው፡፡
ታላቁን የዓድዋ ድል የ125ኛ መታሰቢያ በዓል በመላዉ ኦሮሚያ በተለያዩ ዝግጅቶ ለማክበር ዝግጅቶች መጀመሩንም ገልፀዋል፡፡
በዓሉ “ዓድዋ የኅብረ ብሔራዊ አንድነት አርማ” በሚል መሪ ቃል ይከበራል፡፡
በበዓሉ በአድዋ ዘመቻ በጀግንነት የተዋደቁ ጀግኖች አባቶች የሚታወሱበት የተለያዩ የኪነ ጥበብ ዝግጅቶች እንደሚቀርቡም ነው በማህበራዊ ገፃቸው ይፋ ያደረጉት፡፡
አቶ አዲሱ በአሉ ወንድማችነት እና ህብረ ብሄራዊ አንድነታችንን የሚያጠናክሩ ዉይይቶችን በማድረግ ፣ ለህዳሴ ግድባችን ገቢ በማሰባሰብ እንዲሁም የተለያዩ የአደባባይ ትርዒቶችን በማቅረብ የሚከበር ይሆናል ብለዋል፡፡
የአድዋ ድል የ125ኛ መታሰቢያ በዓል በሁሉም በክልሉ በሚገኙ ሁሉም ዞኖች እና ከተሞች የሚከበር እንደሆነም አስታውቀዋል፡፡
የበዓሉ ማጠቃለያ በክልል ደረጃ መስቀል አደባባይ በደማቅ ስነ ስርዓት የሚከበር ይሆናል ብለዋል፡፡
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

