አዲስ አበባ፣ ጥር 21፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የሀገር መከላከያ ሰራዊት ከአባሉ እስከ ከፍተኛ አመራሩ የኢትዮጵያ ብሄር ብሔረሰቦችን እንዲመስል እና ከወቅቱ ጋር እንዲዘምን ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑን የጦር ሀይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጄኔራል ብርሀኑ ጁላ ተናገሩ ።
ከለውጡ በኋላ ወደ ሰራዊቱ የሚቀላቀሉ ወጣቶች ፍላጎት መጨመሩን የገለፁት ጄኔራል ብርሀኑ ከመላ ሀገሪቱ በተመለመሉ ከፖለቲካ ወገንተኝነት የፀዱና ለሙያው ፍቅርና ክብር ያላቸው ተተኪ ወታደሮችን ለማፍራት ከፍተኛ ስራዎች እየተሰሩ ይገኛሉ ብለዋል ።
በዚህም አበረታች ለውጦች እየተገኙ መሆናቸውን ገልፀዋል፡፡
በተለይም ከዚህ በፊት በውሳኔ ሰጪ ቦታዎችና የተመረጡ ሙያዎች በከፍተኛ ወታደራዊ አመራሩ በአንድ ብሔር ተወላጆች ብቻ ተይዞ መቆየቱን አስታውሰው ከለውጡ በኋላ የማመጣጠን ስራዎች በመሰራታቸው ትልቅ ውጤት ተገኝቶበታል ነው ያሉት ።
ይህም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል፡፡
ሠራዊቱ ዘመኑ ከደረሰበት ቴክኖሎጂ ጋር አብሮ እንዲዘምንም ሁለንተናዊ ተግባራት በመከናወን ላይ እንደሚገኝ ጀነራል ብርሀኑ ጁላ መግለፃቸውን ከመከላከያ ሚኒስቴር ያገኘው መረጃ ያመላክታል።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

