አዲስ አበባ ፣ ጥር 24 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስደተኞች ጉዳይ ከፍተኛ ኮሚሽን ኮሚሽነር ፊሊፖ ግራንዴ ጋር ተወያዩ።
በውይይታቸውም መንግስት በትግራይ ክልል እያደረገ ስላለው የሰብዓዊ ድጋፍ እና ስደተኞችን በማስተናገድ ረገድ ያሉ ጥረቶችን በተመለከተ መክረዋል።
ከዚህ ባለፈም በተለያዩ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ውይይት አድርገዋል።
በወቅቱም መንግስት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስደተኞች ጉዳይ ከፍተኛ ኮሚሽን የሚያደርገውን ድጋፍ ትርጉም ባለው መልኩ ለመጠቀም ቁርጠኛ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አረጋግጠዋል።
ኮሚሽነሩ ባለፉት ቀናት በትግራይ ክልል በሚገኙ የስደተኛ መጠለያ ጣቢያዎች ጉብኝት ማድረጋቸው ይታወቃል።
ኢትዮጵያ ከአፍሪካ ሃገራት ስደተኞችን ተቀብሎ በማስተናገድ በግንባር ቀደምትነት ትቀመጣለች።
በምስክር ስናፍቅ
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

