Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

“የማይስ ኢትዮጵያ” የኮንቬንሽን ቢሮ በይፋ ተመሰረተ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 25 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያን ከዓለም አቀፍ ጉባኤዎች እና ሁነቶች የቱሪዝም ተጠቃሚ ለማድረግ ያስችላል የተባለው “የማይስ ኢትዮጵያ” የኮንቬንሽን ቢሮ በይፋ ተመሰረተ።

ምስረታው ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ እና የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር እና የቱሪዝም ኢትዮጵያ የቦርድ ሰብሳቢ አቶ ሀይለማርያም ደሳለኝ በተገኙ በት ነው ይፋ የሆነው።

ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ቢሮው መመስረቱ ታሪካዊ መሆኑን በመጥቀስ በአግባቡ ከተሰራበት ለውጥ እንደሚያመጣ ተናግረዋል።

አያይዘውም የቢሮው መመስረት የአሁኑ ትውልድ ያለውን ሃገራዊ ማንነት በሚገባ በመረዳት የነገዋ ኢትዮጵያ ላይ የበኩሉን አሻራ እንዲያሳርፍ ያግዛል ብለዋል፡፡

አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ በበኩላቸው የቢሮው መቋቋም ኢትዮጵያ ያሏትን የቱሪዝም ፀጋዎች በመጠቀም በዓለም ያላትን ገፅታ ለመቀየር እንደሚያግዛት ገልጸዋል፡፡

መንግሥት ከዋና ዋና የትኩረት አቅጣጫዎቹ መካከል የቱሪዝም ዘርፉ አንዱ እንዲሆን በማድረጉ ሊመሰገን ይገባዋልም ነው ያሉት፡፡

ኢትዮጵያ በተለይ ባለፉት ሁለት አመታት አዲስ የ”ማይስ” ቱሪዝም መለያ በማዘጋጀት ወደ ዓለም አቀፍ የማይስ ገበያ ለመግባት ስትሰራ ነበር፡፡

ቢሮው በዓለም አቀፍ ደረጃ እያደገ የመጣውን የማይስ ቱሪዝም ወይም የጉባኤ፣ የየጉዞ ማበረታቻ፣ ኮንፈረንሶች፣ ሁነቶች እና አውደ ርዕይ መሰረት ያደረገ ቱሪዝም ኢትዮጵያ ተጠቃሚ እንድትሆን ያስችላታል ተብሏል።

ተቋሙ “በምድረ ቀደምት እንገናኝ” የሚል መሪ ቃል እንዳለው ተገልጿል፡፡

በሶዶ ለማ

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version