Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በህጋዊነት የተመዘገቡ ሁሉም የፖለቲካ ፓርቲዎች የምርጫ መወዳደሪያ ምልክቶቻቸውን  ወሰዱ

አዲስ አበባ፣ ጥር 25፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በህጋዊነት የተመዘገቡ ሁሉም የፖለቲካ ፓርቲዎች የምርጫ መወዳደሪያ ምልክቶቻቸውን ወስደዋል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ 6ተኛው አገር አቀፍ ምርጫን ለማከናወን በጊዜ ሰሌዳው ላይ ካስቀመጣቸው ተግባራት መካከል አንደኛው የፖለቲካ ፓርቲዎች የምርጫ ምልክቶቻቸውን የሚመርጡበት/ የሚያስገቡበት መርሃ ግብር መሆኑ ተመላክቷል

በጊዜ ሰሌዳው መሰረትም  ከጥር 13 ቀን እስከ ጥር 24 ቀን 2013 ዓ.ም ድረስ ፓርቲዎች ምልክት የሚያስገቡበት እና ቦርዱ አጣርቶ የሚያፀድቅበት እንደሆነ ይታወሳል።

በዚህም መሰረት ሁሉም የፖለቲካ ፓርቲዎች የምርጫ መወዳደሪያ ምልክቶቻቸውን የመረጡ ሲሆን በብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ፀድቋል።

በዚህም መሰረት ምርጫ ቦርዱ  የፖለቲካ ፓርቲዎቹ እና ምልክቶቻቸውን በ ፌስቡክ ገጹ ላይ ይፋ አድርጓል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version