አዲስ አበባ፣ ጥር 26፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) በትግራይ ክልል የሰላማዊ ዜጎችን ሞት በተመለከተ በዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን የሚወጡ መረጃዎች ያልተረጋገጡና ካልተሳካ የፖለቲካ ፍላጎት የተነሳ የሚለቀቁ መሆናቸውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መረጃ ማጣሪያው አስታወቀ።
መረጃ ማጣሪያው ባወጣው መግለጫ ህግን በማስከበር እምርጃው ወቅት የተከሰተ ማንኛውም ሞት መንግስት እንደሚያሳዝነው ገልጿል።
የአንድ ግለሰብ ሞትም በጣም ብዙ ነው በማለት በንጹሃን ላይ በሚደርስ ጉዳት ሃዘን እንደሚሰማው በመግለጫው ላይ አስፍሯል።
ሆኖም በነበረው ህግን የማስከበር እርምጃው በመከላከያ ሰራዊት ጥንቃቄ የተሞላበት እቅድ እና ሙያዊ ስነ ምግባር በሰላማዊ ዜጎች ላይ ጉዳት ማጋጠሙን የሚያሳይ መረጃ እንደሌለም ነው የገለፀው።ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

