Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ባለስልጣኑ በ18 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር ስምንት መንገዶችን ለማስገንባት ስምምነት ተፈራረመ

አዲስ አበባ፣ ጥር 26፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን በ18 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር ስምንት መንገዶችን ለማስገንባት ስምምነት ተፈራረመ።

በዛሬው ዕለት ስምምነት የተፈረመባቸውን መንገዶች ጨምሮ በ2013 ስድስት ወራት ብቻ በ43 ነጥብ 3 ቢሊየን ብር የሚገነቡ 21 የመንገድ ፕሮጀክቶች  ፊርማ መከናወኑ ተጠቁሟል።

አጠቃላይ የመንገድ ፕሮጀክቶቹ እርዝማኔ 1 ሺህ 774 ኪሎ ሜትር የሚሸፍኑ ሲሆን÷ የ20ዎቹ መንገዶችን የግንባታ ወጪ የኢትዮጵያ መንግስት የሚሸፍን ይሆናል ተብሏል።

የቀሪውን አንድ የመንገድ ፕሮጀክት በጃፓኑ አለማቀፍ ተራድኦ ድርጅት (JICA) ከአፍሪካ ልማት ባንክ (AfDB)እና ከአለም ባንክ በተገኘ ብድር እንዲሁም በኢትዮጵያ መንግስት በተያዘ በጀት የሚከናወን መሆኑ ተነግሯል።

መንገድ ግንባታዎቹን የውል ስምምነት የተፈረመው ከሃገር በቀል  እና ከውጭ ሃገራት የስራ ተቋራጮች ጋር ነው።

በይስማው አደራውከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version