አዲስ አበባ፣ ጥር 28፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ አፈጻጸም 78 ነጥብ 3 መድረሱን የውሃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር ገለጸ።
ሚኒስቴሩ ባለፉት ስድስት ወራት ያከናወናቸውን ተግባራትንና የህዳሴ ግድቡን የግንባታ ሂደት በተመለከተ መግለጫ የሰጡት የውሃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር ዶክተር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ እንደገለጹት፤ የግድቡ ግንባታ የሲቪል ስራዎች አፈጻጸም 91 በመቶ ደርሷል።
አጠቃላይ የግድቡ ግንባታ አፈጻጸም ደግሞ 78 ነጥብ 3 በመቶ መድረሱን አመልክተዋል።
በቀጣይ ወራት የግድቡን ሁለተኛ ዙር የውሃ ሙሌት ለማሳካት እንደሚሰራ መጠቆማቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

